am_tn/psa/050/007.md

1.0 KiB

ስለ መሥዋዕቶችህ አልነቅፍህም

“እነቅፍሃለሁ፣ ስለ መሥዋዕቶችህ ግን አይደለም”። እግዚአብሔር የሚወቅሳቸው በመሥዋዕቶቻቸው ምክንያት እንዳልሆነ ያስታውቃቸዋል።

መንቀፍ

አንድ ሰው የማይገባውን ነገር እንዳደረገ ለእርሱ መንገር

የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህ ሁልጊዜ በፊቴ ናቸው

እግዚአብሔር ስለ መሥዋዕታቸው ለምን እንደማይወቅሳቸው ይኼ ያብራራል። “ሁልጊዜ በፊቴ ናቸው” የሚለው ሐረግ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መሆንን የሚያመለክት ሲሆን ትርጉሙም የእርሱ የሆነው ሕዝብ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ሁልጊዜ እያቀረቡለት ነው የሚል ይሆናል። አ.ት፡ “እናንተ ሁልጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕት እያቀረባችሁልኝ ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)