am_tn/psa/050/001.md

1.6 KiB

የአሳፍ መዝሙር

“ይህ አሳፍ የጻፈው መዝሙር ነው”

ኃያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር

ደራሲው ስለ እግዚአብሔር ለመናገር የተለያዩ ሦስት ስሞችን ይጠቀማል።

ምድርን ጠርቷል

እዚህ ጋ፣ “መሬት” የሚለው ቃል በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል። አ.ት፡ “ሰዎችን ሁሉ ጠርቷል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ

ይህ ሐረግ ፀሐይ የምትወጣበትን የምስራቅ አቅጣጫና የምትገባበትን የምዕራብ አቅጣጫ ያመለክታል። ጸሐፊው በምድር ላይ ሁሉን ስፍራ እንዲወክል እነዚህን ሁለት ጽንፎች ይጠቀማል። አ.ት፡ “በምድር ላይ በሁሉም ስፍራ” (See: Merism)

የውበት መደምደሚያ ጽዮን

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ውበቷ ፍጹም የሆነ ጽዮን” ወይም 2) “እጅግ የተዋበችው ከተማ ጽዮን” የሚሉት ናቸው።

እግዚአብሔር አበራ

ጸሐፊው እግዚአብሔርን እንደሚያበራ ብርሃን አድርጎ ይናገራል። ይህ ሰዎች ስለ ክብሩ እንዲያውቁ እግዚአብሔር እንደሚያደርግ ያመለክታል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር ክብር እንደ ብርሃን ያበራል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)