am_tn/psa/049/018.md

1.9 KiB

ነፍሱን ባርኳል

እዚህ ጋ “ነፍስ” የሚለው ቃል የሰውን ሁለንተና ያመለክታል። የዚህ ሐረግ ትርጉም፣ በሀብቱ ምክንያት ራሱን ደስተኛና ስኬታማ አድርጎ ይቆጥራል የሚል ነው። አ.ት፡ “ራሱን ‘እንኳን ደስ ያለህ’ ብሏል” (See: Synecdoche እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ለራስህ በምትኖርበት ጊዜ ሰዎች ያመሰግኑሃል

እዚህ ጋ፣ ጸሐፊው ሰዎች በዓለማዊው መስፈርት ስኬታማ ስለሆኑ ስለ ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደሚናገሩ ጠቅለል ያለ አባባል አቅርቧል።

ለራስህ ስትኖር

ይህ ሐረግ በዓለማዊው መስፈርት በስኬታማነት መኖርን ያመለክታል። አ.ት፡ “ለራስህ መልካሙን አድርግ” ወይም “በስኬት ኑር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ወደ አባቶቹ ትውልድ ይሄዳል

“የአባቶቹ ትውልድ ወዳለበት ይሄዳል”። ይህ የተሻለ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ሀብታሙ ሰው ይሞትና በመቃብር ውስጥ ከአባቶቹ ጋር ይገናኛል የሚል ነው። አ.ት፡ “መቃብር ውስጥ ከአባቶቹ ጋር ይገናኛል” (See: Euphemism)

ዳግመኛ ብርሃንን ከቶ አያዩም

በውስጠ ታዋቂ ያለው “እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሀብታሞችንና አባቶቻቸውን ነው። “ብርሃን” የሚለው ቃል ፀሐይን ያመለክት ይሆናል ወይም በዘይቤአዊ አነጋገር ሕይወት ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “ዳግመኛ ፀሐይን ከቶ አያዩም” ወይም “ዳግመኛ ከቶ በሕይወት አይኖሩም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)