am_tn/psa/049/014.md

2.2 KiB

እንደ በጎች

ጸሐፊው የሚሞቱትን ሰዎች ሁሉ ከበግ መንጋ ጋር ያነጻጽራቸዋል። ልክ አራጁ ሊያርዳቸው በሚወስንበት ጊዜ በጎች ማምለጥ እንደማይችሉ ሰዎችም የሚሞቱበት ጊዜ ሲደርስ አያመልጡም። (See: Simile)

ተወስነዋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ወስኗቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ሞት እረኛቸው ይሆናል

ጸሐፊው ሞትን ወደ መቃብር እንደሚመራቸው ሰው በመቁጠር ስለሚሞቱ ሰዎች ይናገራል። አ.ት፡ “እረኛ በጎችን ወደሚታረዱበት እንደሚወስዳቸው ሞት ይወስዳቸዋል” (ሰውኛ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጠዋት

እዚህ ጋ “ጠዋት” የሚለው ቃል ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን እግዚአብሔር ጻድቃንን ነጻ የሚያወጣበትንና ከክፉ ሰዎች የሚያድንበትን ጊዜ ያመለክታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰውነታቸው በሲዖል ይቃጠላል

ሲዖል ሰው ወይም እንስሳ የሆነ ይመስል ጸሐፊው የሙታን ስፍራ ስለሆነው ስለ እርሱ ይናገራል። ስለ ሬሳ መበስበስ ሲናገርም ሲዖል እነርሱን እንደሚበላቸው አድርጎ ይናገራል። (ሰውኛ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሕይወቴን ከሲዖል ኃይል ያድናታል

ጸሐፊው ስለ ሲዖል ሲናገር በሚሞቱት ላይ ኃይል እንዳለው ሰው አድርጎ ይገልጸዋል። ከዐውዱ አንጻር ይህ ኃይል የሙታንን አካል እንደሚበላ ያመለክታል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሕይወቴን ያድናታል

እዚህ ጋ “ሕይወት” የሚለው ቃል የሰውን ሁለንተና ያመለክታል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያድነኛል” (See: Synecdoche)