am_tn/psa/048/009.md

2.1 KiB

የቃል ኪዳን ታማኝነትህ

የነገር ስም የሆነው “ታማኝነት” እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ለቃል ኪዳንህ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንክ” ወይም “ከቃል ኪዳንህ የተነሣ ለእኛ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንክ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በመቅደስህ መካከል

“በመቅደስህ ውስጥ እያለን”

እንደ ስምህ ሁሉ … ምስጋናህም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው

እዚህ ጋ፣ “ስም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ባህርይና ዝና ይወክላል። ሁለቱ ሐረጎች የእግዚአብሔርን የታላቅነቱን ዝና ሰዎች እርሱን እንዴት ከፍ ባለ ሁኔታ ያመሰግኑት እንደሆነ ያነጻጽራሉ። አ.ት፡ “ስምህ እጅግ ታላቅ ነው … በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርቡልሃል” ወይም “በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ስለ አንተ ሰምተዋል … ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ያመሰግኑሃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን በዓለም ላይ በሁሉም ስፍራ ማለት ነው። ይህንን በመዝሙር 46፡9 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል

ጸሐፊው ጽድቅን እግዚአብሔር በእጁ ሊይዘው እንደሚችለው ቁስ አድርጎ ይናገራል። እዚህ ጋ፣ “እጅ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ኃይልና የመግዛት ሥልጣኑን ያመለክታል። አ.ት፡ “በጽድቅ ትገዛለህ” ወይም “አንተ ስትገዛም ጻድቅ ነህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)