am_tn/psa/048/007.md

2.3 KiB

በምስራቁ ንፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) እግዚአብሔር በታላቅ ንፋስ ስለሚያጠፋቸው እንደሚናወጡ መርከቦች፣ ይህ ጸሐፊው የንጉሡን መፍራት የሚገልጽበት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በምስራቁ ንፋስ በሰባበርካቸው ጊዜ የተርሴስ መርከቦች እንደተናወጡ እነርሱ በፍርሐት ተናወጡ” ወይም 2) ይህ ደራሲው የእግዚአብሔርን ታላቅ ኃይል የሚገልጽበት ምልክት ነው የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Apostrophe የሚለውን ተመልከት)

የምስራቅ ንፋስ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ከምስራቅ የሚነፍሰው ንፋስ” ወይም 2) “ከባድ ንፋስ” የሚሉት ናቸው።

የተርሴስ መርከቦች

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ ይህ የሚያመለክተው 1) ወደዚያ የሚጓዙ ወይም በተርሴስ የሚሠሩ መርከቦችን ወይም 2) የትኛውንም በውቅያኖስ ላይ መጓዝ የሚችል ትልቅ መርከብን ነው የሚሉት ናቸው።

እንደ ሰማነው

እግዚአብሔር ባለፉት ዘመናት ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች መስማታቸውን ያመለክታል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ስላደረጋቸው ታላላቅ ነገሮች እንደሰማነው” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

እኛም ደግሞ አይተናል

ይህ ማለት የሰሟቸው ነገሮች እውነት ስለመሆናቸው ማረጋገጫውን አይተዋል። አ.ት፡ “አሁንም እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ሲሠራ አይተናል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

በሰራዊት ጌታ ከተማ፣ በአምላካችን ከተማ

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች የሚያመለክቱት ኢየሩሳሌምን ነው። አ.ት፡ “በሰራዊት ጌታ፣ በአምላካችን ከተማ” (See: Paral- lelism)

ያጸናታል

“የተጠበቀች ያደርጋታል”። እዚህ ጋ፣ “ማጽናት” የሚለው ቃል ትርጉም አንድን ነገር ማቆየት እና መጠበቅ ማለት ነው።