am_tn/psa/048/001.md

2.3 KiB

የቆሬ ልጆች መዝሙር

“የቆሬ ልጆች የጻፉት መዝሙር ይህ ነው”

ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ከፍ ያለ ምስጋና ያቅርቡለት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራው ላይ

ይህ በጽዮን ተራራ ላይ የተሠራችውን ኢየሩሳሌምን ያመለክታል።

የአምላካችን ከተማ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “አምላካችን የሚኖርበት ከተማ” ወይም 2) “የአምላካችን የሆነው ከተማ” የሚሉት ናቸው።

በከፍታው ላይ የተዋበው

“የተዋበና ከፍ ያለ”። “ከፍታ” የሚለው ቃል የጽዮን ተራራ ምን ያህል ከፍ ያለ መሆኑን ያመለክታል።

የምድር ሁሉ ደስታ ጽዮን ናት

እዚህ ጋ፣ “ምድር” የሚለው ቃል በምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ ያመለክታል። “ደስታ” የሚለው ቃል እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የጽዮን ተራራ በምድር ለሚኖሩ ሁሉ ደስታን ይሰጣል” ወይም “በጽዮን ተራራ ምክንያት በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይደሰታሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በሰሜን በኩል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ ይህ ሐረግ 1) የሰሜንን አቅጣጫ ያመለክታል ወይም 2) “የእግዚአብሔር ተራራ” የሚል ትርጉም ላለው የጽዮን ተራራ ሌላኛው ስሙ ነው የሚሉት ናቸው።

እንደ መሸሸጊያ በሆኑት ቤተ መንግሥቶቿ እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል

ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር ሲናገር ሰዎች ለደህንነታቸው እንደሚደበቁበት ስፍራ አድርጎ ይገልጸዋል። አ.ት፡ “በጽዮን ተራራ ቤተ መንግሥቶች ውስጥ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ደህንነትን የሚሰጥ ሆኖ ራሱን ገልጧል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)