am_tn/psa/047/003.md

2.6 KiB

ሕዝቦችን ከበታቻችን፣ ሀገራትንም ከእግሮቻችን በታች ያስገዛል

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች ተመሳሳዮች ናቸው፤ ትርጉሙም፣ እስራኤል ጠላቶቻቸውን እንዲያሸንፉ እግዚአብሔር አስችሏቸዋል ማለት ነው። (See: Parallelism)

ያስገዛል

ድል ማድረግና በሌላው ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ማድረግ

ከበታቻችን … ከእግሮቻችን በታች

ጸሐፊው ሌሎች ሕዝቦችን ስለ ማሸነፍ ሲናገር እነዚያ ሕዝቦች ከእግሮቻቸው ሥር እንደተደረጉ ያህል አድርጎ ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ርስታችንን ይመርጥልናል

ጸሐፊው የእስራኤልን ምድር ቋሚ ንብረት እንዲሆናቸው እግዚአብሔር ለሕዝቡ በርስትነት እንደሰጣቸው አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ይህችን ምድር ርስት እንዲሆነን ይመርጥልናል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የያዕቆብ ክብር

እዚህ ጋ፣ “ክብር” የሚለው ቃል የኩራትን ምንጭ ያመለክታል፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስት አድርጎ የሰጣቸውን ምድርም ይወክላል። አ.ት፡ “ያዕቆብ የሚኮራበት ምድር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የወደደውን ያዕቆብን

“ያዕቆብ” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምላክ በዕልልታ ዐረገ

ጸሐፊው እግዚአብሔር ሕዝቦችን ድል ስለማድረጉ ሲናገር እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ በቤተ መቅደስ በሚገኘው ዙፋን ላይ እንደሚቀመጥ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ሕዝቡ ዕልል እያሉ እግዚአብሔር ወደ መቅደሱ ዐረገ” ወይም “ሕዝቡ ዕልል እያሉ እግዚአብሔር ዙፋኑ ላይ ተቀመጠ” (ዘይቤአዊ አነጋገር፣ እና Assumed Knowledge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ

ይህ ሐረግ ቀደም ሲል ከነበረው ሐረግ ጋር ተመሳሳይ ነው። ለግልጽነቱ ግሥ ሊጨመርበት ይችላል። አ.ት፡ “ሕዝቡ መለከቶቹን እየነፉ እግዚአብሔር ዐረገ” (See: Parallelism and Ellipsis)