am_tn/psa/046/004.md

1.7 KiB

በምንጮቹ የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ የሚያሰኝ ወንዝ አለ

የወራጅ ወንዝ ሥዕል የእግዚአብሔርን ከተማ ሰላምና ብልጽግና ያሳያል። (See: Symbolic Language)

የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ የሚያሰኝ

“የእግዚአብሔር ከተማ” የሚለው ሐረግ ኢየሩሳሌምን ሲያመለክት በከተማይቱ የሚኖሩትን ሰዎችም ይወክላል። አ.ት፡ “በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሰዎች ደስ ያሰኛቸዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ልዑሉ የሚያድርበት ቅዱሱ ስፍራ

ይህ ሐረግ “የእግዚአብሔር ከተማ”ን ያብራራል። አ.ት፡ “ልዑሉ የሚኖርበት ቅዱሱ ስፍራ” (See: As- sumed Knowledge and Implicit Information)

በመካከሏ፤ … ይረዳታል፣ አትናወጥም

“እርሷን” እና “እርሷ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት “የእግዚአብሔር ከተማ”ን ነው።

አትናወጥም

እዚህ ጋ፣ “አትናወጥም” የሚለው ቃል በመዝሙሩ ቁጥር 2 ላይ “አትነቀነቅም” ተብሎ ከተተረጎመው ቃል ጋር አንድ ነው። ጸሐፊው፣ ኢየሩሳሌም በወታደሮች መፍረሷን የመሬት መንቀጥቀጥ እንዳጠፋት አድርጎ ይናገራል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ምንም ነገር እርሷን ሊያጠፋት አይችልም” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)