am_tn/psa/045/005.md

2.3 KiB

ሕዝቦች ከበታችህ ይወድቃሉ

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ንጉሡ ጠላቶቹን ማሸነፉን ነው። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ሕዝቦች ተማርከው እግርህ ላይ ይወድቃሉ” ወይም 2) “ሕዝቦች እግርህ ስር ይሞታሉ” የሚሉት ናቸው።

ቀስቶችህ በንጉሡ ጠላቶች ልብ ውስጥ ናቸው

“ቀስቶችህ የጠላቶችህን ልብ ወግቷል”። ጸሐፊው ንጉሡን በማመልከት በሦስተኛ መደብ የሚናገረው ለንጉሡ ነው።

. . . ዙፋንህ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ነው

“ዙፋን” የሚለው ቃል የንጉሡን መንግሥትና አገዛዝ ይወክላል። አ.ት፡ “መንግሥትህ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ነው” ወይም “ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ትነግሣለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሆይ ዙፋንህ

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ “እግዚአብሔር” የሚለው ቃል 1) የእግዚአብሔር ወኪል የሆነው የንጉሡ መጠሪያ ነው ወይም 2) “ዙፋን” የሚለውን ቃል “እግዚአብሔር የሰጠህ መንግሥት” ለሚለው ተስማሚ ያደርገዋል የሚሉት ናቸው።

በትረ - መንግሥትህ የፍትሕ በትረ - መንግሥት ነው

“በትረ - መንግሥት” የሚለው ቃል መንግሥቱን ለማስተዳደር ያለውን የንጉሡን ሥልጣን ይወክላል። አ.ት፡ “መንግሥትህን በፍትሓዊነት ታስተዳድራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምላክህ እግዚአብሔር በደስታ ዘይት ቀብቶሃል

ጸሐፊው ስለ ደስታ ሲናገር እግዚአብሔር ንጉሡን ለመቀባት እንደተጠቀመበት ዘይት አድርጎ ይገልጸዋል። እግዚአብሔር እርሱን መቀባቱ ንጉሥ እንዲሆን እንደ መረጠው ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ንጉሥ አድርጎ በሾመህ ጊዜ በጣም ደስ አሰኘህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Symbolic Action የሚለውን ተመልከት)