am_tn/psa/045/003.md

2.3 KiB

ሰይፍህን በጎንህ ታጠቀው

ተዋጊዎች ሰይፋቸውን በወገባቸው ዙሪያ ባለው ቀበቶ በሚንጠለጠለው ሰገባ ውስጥ ይታጠቁት ነበር። ሰይፉ በጎናቸው በኩል ይቀመጣል። ይህ ሐረግ አንድ ሰው ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት ይገልጻል። አ.ት፡ “ራስህን ለጦርነት አዘጋጅ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

በድል አድራጊነት ገስግስ

ጸሐፊው ንጉሡ በፈረሱ ወይም በሰረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ድል እንዲገሰግስ ይነግረዋል

በእውነተኝነትህ፣ በየዋህነትህና በጽድቅህ ምክንያት

የነገር ስም የሆኑት “እውነተኝነት”፣ “የዋህነት” እና “ጽድቅ” እንደ ቅጽል ሊነገሩ ይችላሉ። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) እነዚህ የኃያል ሰው መለያ ናቸው። አ.ት፡ “አንተ እውነተኛ፣ የዋህና ጻድቅ ስለሆንክ” ወይም 2) እነዚህ ለሚያስተዳድረው ሕዝብ ሊያቆይላቸው የሚዋጋላቸው መልካም ባህርያት ናቸው። አ.ት፡ “ለእውነተኝነት፣ ለየዋህነትና ለትክክለኝነት ለመዋጋት” የሚሉት ናቸው። (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ቀኝ እጅህ አስፈሪ ነገሮችን ያስተምርሃል

አብዛኞቹ ወታደሮች በሚዋጉበት ጊዜ ሰይፋቸውን በቀኝ እጆቻቸው ይይዙ ነበር። እዚህ ጋ “ቀኝ እጅ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ጸሐፊው ስለ አንድ፣ ከጦርነት ያገኘውን ልምድ ለንጉሡ ሊያስተምር ስለ ቻለ ሰው፣ የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “በብዙ ጦርነቶች በመዋጋት ታላላቅ ወታደራዊ ጀብዱዎችን ለመፈጸም ትማራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

አስፈሪ ነገሮች

“አስደናቂ ሥራዎችን”። ይህ ጠላቶቹ እንዲፈሩትና ተባባሪዎቹ እንዲያከብሩት የሚያስደርጋቸውን ወታደራዊ ድሎች ያመለክታል።