am_tn/psa/045/001.md

3.1 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

ለሾሻኒም የተዘጋጀ

ለሾሻኒም የተዘጋጀ

የቆሬ ልጆች መዝሙር

“ይህ የቆሬ ልጆች የጻፉት መዝሙር ነው” ይህ አንድን ሙዚቃ ስልት ወይም ቅኝት ሳያመለክት አይቀርም። አንዳንድ ጊዜ “ለ’ጽጌረዳ’ ቅኝት የተዘጋጀ” ተብሎ ተተርጉሟል። ይህንን በመዝሙር 32፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የፍቅር መዝሙር

“የፍቅር መዝሙር”

ልቤ መልካም አሳብ ሞልቶት ያፈስሳል

ጸሐፊው ፈሳሽ ሞልቶት እንደሚያፈስ ዕቃ ስለ ልቡ ይናገራል። “ልብ” የሚለው ቃል በሚዘምረው መዝሙር የተደሰተ ስሜቱን ይወክላል። አ.ት፡ “ስለ መልካሙ አሳብ ደስታ ተሰምቶኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መልካም አሳብ

“የከበረ ርዕሰ ጉዳይ” ወይም “ያማረ ቃል”። ይህ የሚያመለክተው እርሱ የጻፈውን መዝሙር ነው።

የተቀናበረ

የተጻፈ ወይም የተደረሰ መዝሙር

ምላሴ የዝግጁ ጸሐፊ እስክሪብቶ ነው

ጸሐፊው እስክሪብቶ ብሎ የሚናገረው ስለ ምላሱ ነው። ልምድ ያለው ጸሐፊ ቃላትን እንደሚጽፍ እርሱ ቃላትን በብልሃት ይናገራል። አ.ት፡ “ምላሴ በደንብ እንደሚጽፍ ሰው እስክሪብቶ ነው” ወይም “ልምድ ያለው ጸሐፊ ቃላትን መጻፍ እንደሚችል ሁሉ እኔም ቃላትን በብልሃት እናገራለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከሰው ልጆች ይልቅ ውብ ነህ

ይህ ሐረግ ንጉሡ ከማንም ይልቅ ማራኪ ስለመሆኑ አጽንዖት ለመስጠት የተነገረ ግነት ነው። “የሰው ልጆች” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ሰዎችን ሁሉ ያመለክታል። አ.ት፡ “አንተ ከየትኛውም ወንድ ይልቅ መልከ መልካም ነህ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በከንፈሮችህ ላይ ጸጋ ይፈስሳል

አንድ ሰው የንጉሡን ከንፈሮች ለመቀባት የተጠቀመበትን ዘይት በሚመስል መልኩ ጸሐፊው የሚናገረው ስለ ጸጋ ነው። “ከንፈሮች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የንጉሡን ንግግር ነው። የሐረጉ ትርጉም፣ ንጉሡ አንደበተ ርቱዕ ነው የሚል ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው ከንፈሮችህን በዘይት የቀባቸው ይመስላል” ወይም “አንደበተ ርቱዕ ነህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)