am_tn/psa/043/005.md

1.4 KiB

ነፍሴ ሆይ፣ ለምን አቀረቀርሽ? ለምንስ በውስጤ ተረበሽሽ?

ደራሲው ራሱን ወደሚወክልበት “ነፍሱ” ይኸውም ውስጣዊ ማንነቱ ያመለክታል። ራሱን ለመውቀስ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠይቃል። ይህንን በመዝሙር 42፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ማቀርቀር አልነበረብኝም። መጨነቅ አልነበረብኝም” (See: Imperatives - Other Uses)

ማቀርቀር

ጸሐፊው ነፍሱ የጎበጠች ይመስል የሚናገረው ስለ መጫጫን ወይም ተስፋ መቁረጥ ነው። ይህንን በመዝሙር 42፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ተስፋ ቆርጫለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእግዚአብሔር ተስፋ አድርጊ

ጸሐፊው ለነፍሱ መናገሩንና በእግዚአብሔር እንድትታመን ማዘዙን ቀጥሏል። ይህንን በመዝሙር 42፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

አምላኬና ድነቴ

“ድነቴ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል። አስፈላጊ ከሆነ ሁለቱ ሐረጎች ሊጣመሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “የሚያድነኝ አምላኬ” (See: Doublet)