am_tn/psa/042/007.md

2.1 KiB

በፏፏቴህ ድምፅ አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል

“ጥልቅ” የሚለው ቃል ጥልቅ የሆነውን የውሃ አካል የሚያመለክት ሲሆን እዚህ ጋ ሊሆን የሚችለው ከአርሞንኤም ተራራ ወደ ታች የሚወርደውን ምንጭ ነው። ሰዎች ከተራራው ላይ ሲወርዱ የሚያሰሙትን እንቅስቃሴ ለእርስ በእርስ እንደሚያወሩ አድርጎ ጸሐፊው ስለ ውሃው አወራረድ ይናገራል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ሞገድህና … ሁሉ በላዬ ላይ አልፏል

ደራሲው እጅግ አስከፊ የሆነበትን አጋጣሚና ሐዘኑን አንዱ ሞገድ ከሌላው ሞገድ ጋር እያላጋው ጥልቅ ውሃ እንዳሰጠመው ያህል አድርጎ ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሞገድህና ማዕበልህ

“ማዕበል” የሚለው ቃል “ሞገድ” ለሚለው ተለዋጭ ቃል ነው። ሁለቱ ቃላት በአንድነት በሞገዱ ታላቅነት ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ታላላቅ ሞገዶችህ ሁሉ” (See: Doublet)

እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታማኝነቱን በቀን ያዛል

ከእርሱ ጋር እንዲኖር የሚያዘው ሰው የሆነ ይመስል ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታማኝነት ይናገራል። የነገር ስም የሆነው “ታማኝነት” እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታማኝነቱን በቀን ያሳየኛል” ወይም “እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ምን ያህል ታማኝ እንደሆነ በቀን ያሳየኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መዝሙሩን

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “የሚሰጠኝ መዝሙር” ወይም “ስለ እርሱ የሆነውን መዝሙር” የሚሉት ናቸው።

የሕይወቴ አምላክ

“ሕይወት የሚሰጠኝ አምላክ”