am_tn/psa/042/005.md

1.8 KiB

ነፍሴ ሆይ፣ ለምን አቀረቀርሽ? ለምንስ በውስጤ ተረበሽሽ?

ደራሲው ራሱን ወደሚወክልበት “ነፍሱ” ይኸውም ውስጣዊ ማንነቱ ያመለክታል። ራሱን ለመውቀስ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠይቃል። አ.ት፡ “ማቀርቀር አልነበረብኝም። መጨነቅ አልነበረብኝም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና Synecdoche የሚለውን ተመልከት)

ማቀርቀር

ጸሐፊው ነፍሱ የጎበጠች ይመስል የሚናገረው ስለ መጫጫን ወይም ተስፋ መቁረጥ ነው። አ.ት፡ “ተስፋ ቆርጫለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእግዚአብሔር ተስፋ አድርጊ

ጸሐፊው ለነፍሱ መናገሩንና በእግዚአብሔር እንድትታመን ማዘዙን ቀጥሏል። (See: Imperatives - Other Uses)

አምላኬ ሆይ፣ ነፍሴ

ጸሐፊው ስለ ነፍሱ ለእግዚአብሔር መናገር ይጀምራል።

አስብሃለሁ

የዚህ ሐረግ ትርጉም ማስታወስ ወይም ስለ አንድ ነገር ማሰብ ማለት ነው። አ.ት፡ “ስለ አንተ አስባለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የዮርዳኖስ ምድር

ይህ ምናልባት የዮርዳኖስ ወንዝ መነሻ የሆነውን ሰሜናዊ እስራኤል ያመለክት ይሆናል። አ.ት፡ “የዮርዳኖስ ወንዝ መነሻ ምድር” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ጫፍ

የተራራ ጫፍ

የሚዛር ኮረብታ

ይህ በአርሞንኤም ተራራ ስር ያለ የኮረብታ ስም ነው። (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)