am_tn/psa/041/010.md

2.2 KiB

እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ግን ማረኝ፣ አንሣኝም

ይህ ልመና ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህን ማረኝና አንሣኝ” (See: Statements - Other Uses)

አንሣኝ

ይህ ማለት ከአልጋው ላይ እንዲያነሣው ወይም ከበሽታው እንዲያገግም እንዲያደርገው ነው። አ.ት፡ “ጤነኛ አድርገኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

መልሼ እንድከፍላቸው

ጸሐፊው የሚናገራው የተበዳራቸውን ይመልስላቸው ይመስል ጠላቶቹን ስለ መበቀል ነው። አ.ት፡ “እንድበቀላቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጠላቴ ድል አላደረገኝምና በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ

“በዚህ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጸሐፊው ቀጥሎ የሚናገረውን ነው። ለግልጽነት እንዲረዳ ሐረጉ ቦታው ሊቀያየር ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቴ ድል ስለማያደርገኝ በእኔ ደስ እንደሚልህ አውቃለሁ” (የሁነቶች ቅደም ተከተል የሚለውን ተመልከት)

ጠላቴ ድል አላደረገኝምና በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ

እግዚአብሔር ገና ስላልፈወሰው ይህ የወደፊቱን በሚያመለክት ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቶቼ ድል እንዳያደርጉኝ ካስቻልከኝ በእኔ እንደተደሰትክ አውቃለሁ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

በቅንነቴ ትደግፈኛለህ

“በቅንነቴ ምክንያት ትደግፈኛለህ”

በፊትህ ትጠብቀኛለህ

ጸሐፊው እግዚአብሔር እርሱን ማየት በሚችልበትና እርሱም የእግዚአብሔርን ፊት ለማየት በሚችልበት ስፍራ እንደተገኘ ያህል በእግዚአብሔር ሀልዎት ውስጥ ስለመሆን ይናገራል። አ.ት፡ “ከአንተ ጋር ታቆየኛለህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)