am_tn/psa/041/004.md

1.6 KiB

ስሙ የሚደመሰሰው

የአንድ ሰው ስም ሞተ ማለት ሰዎች በሕይወት ኖሮ እንደነበር ይረሱታል ማለት ነው። አ.ት፡ “ስሙ የሚደመሰሰው መቼ ነው” ወይም “ሰዎች ስለ እርሱ የሚረሱት መቼ ነው” (Ellipsis እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ጠላቴ ሊያየኝ ከመጣ

“ጠላቴ” የሚለው ቃል አንድን የታወቀውን ጠላት ማለት ሳይሆን በጥቅሉ የትኛውንም ጠላት ያመለክታል።

እርሱ ከንቱ ነገሮችን ይናገራል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) ትርጉም የለሽ ነገሮችን ይናገራል” ወይም 2) ጠላቶቹ ወዳጆቹ ሳይሆኑ እንደሆኑ እንዲያስብ የሚያስደርገውን ነገር ይናገራሉ የሚሉት ናቸው። አ.ት፡ “የሚያሳስቱ ነገሮችን ይናገራል” ወይም “ስለ እኔ የሚገዳቸው ያስመስላሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ልቡ ለጥፋቴ የሚሆነውን ለራሱ ያከማቻል

ጠላቶቹ የእርሱን ክፉ ነገሮች ሁሉ ለማጥናት ይሞክራሉ። እዚህ ጋ “ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። መጥፎ ሁኔታዎች ሊከማቹ እንደሚችሉ ቁሶች ተደርገው ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “ለጥፋቴ የሚሆነውን ሁሉ ለማጥናት ይሞክራሉ” (Synecdoche እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)