am_tn/psa/041/001.md

1.4 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚናገረው ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) የመዝሙሩ ስልት የዳዊትን መዝሙር ይመስላል የሚሉት ናቸው።

እርሱ … እርሱን … የእርሱ

እነዚህ ቃላት ስለ ደካሞች የሚገደውን ማንኛውንም ሰው ያመለክታሉ።

ደካማው

“ደካሞች ሰዎች” ወይም “ድኾች ሰዎች”

በመከራው አልጋ ላይ እግዚአብሔር ይደግፈዋል

“የመከራ አልጋ” የሚለው ሐረግ አንድ ሰው ታሞ በአልጋው ላይ የሚተኛበትን ጊዜ ያመለክታል። አ.ት፡ “ታሞ አልጋው ላይ በሚሆንበት ጊዜ እግዚአብሔር ይደግፈዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሕመም አልጋውን የፈውስ አልጋ ታደርግለታለህ

“የፈውስ አልጋ” የሚለው ሐረግ አንድ ሰው በአልጋው ላይ በማረፍ ከሕመሙ የሚያገግምበትን ጊዜ ያመለክታል። አ.ት፡ “አንተ እግዚአብሔር፣ ከሕመሙ ትፈውሰዋለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)