am_tn/psa/039/010.md

1.4 KiB

እኔን ማቁሰልህን ተው

እግዚአብሔር ጸሐፊውን መቅጣቱ ልክ በጦር መሣሪያ እግዚአብሔር እንዳቆሰለው ተደርጎ ተነግራል። አ.ት፡ “እባክህን እኔን መቅጣትህን ተው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እኔ ዝዬአለሁ

“ፈጽሞ ተሸንፌአለሁ”

የእጅህ ምት

እግዚአብሔር ጸሐፊውን መቅጣቱ ልክ እግዚአብሔር በቡጢ እንደመታው ተደርጎ ተነግራል። እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ፍርድ ነው። አ.ት፡ “ፍርድህ በእኔ ላይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንደ ብል የተመኟቸውን ነገሮች በላህ

ብል የጨርቅን ቁራጭ እንደሚበላው እግዚአብሔር የከበረ የሚሉትን ነገራቸውን ይወስድባቸዋል። አ.ት፡ “ብል ጨርቅን እንደሚበላ የሚመኟቸውን ነገሮች ይበላል” (See: Simile)

ሰዎች ሁሉ እንደ ተን ብቻ ናቸው

ጸሐፊው የሰዎችን ደካማነት ፈጥኖ ከሚጠፋ ጭጋግ ጋር በማመሳሰል ይናገራል። አ.ት፡ “ሁሉም ፈጽሞ ተሰባሪ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)