am_tn/psa/039/004.md

1.7 KiB

የሕይወቴ ማብቂያ … የቀኖቼ ርዝመት

በመሠረቱ እነዚህ ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ነው። (See: Parallelism)

አላፊ ጠፊ መሆኔን አሳየኝ

“ሕይወቴ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አሳየኝ” ወይም “በቶሎ የምሞትበትን ጊዜ አሳየኝ”

የእጄን እርዝመት ያህል ብቻ

ጸሐፊው የሕይወት ዘመኑ በእጁ እርዝመት ሊለካ እንደሚችል አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “በጣም አጭር ጊዜ ብቻ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሕይወት ዘመኔ በፊትህ እንደ ኢምንት ነው

ይህ ንጽጽር የሚናገረው የጸሐፊው የሕይወት ዘመን እርዝማኔ የማይሰነብት፣ አጭር መሆኑን ነው። ይህ ዕድሜው ምን ያህል አጭር እንደሚሆን አጽንዖት ለመስጠት የተነገረ ግነት ነው። አ.ት፡ “የሕይወቴ እርዝመት በየትኛውም ጊዜ ሊያበቃ የሚችል ነው” (Simile፣ ግነትና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

በእርግጥ እያንዳንዱ ሰው እስትንፋስ ብቻ ነው

ሕይወት አጭር ነው፤ ዘማሪው በዚህ ስፍራ ዕጥረቱ አንድ ሰው ትንፋሹን አንድ ጊዜ የሚተነፍስበትን ያህል እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “የሰዎች የሕይወት ዘመን ልክ አንድ ሰው ከሚተነፍሰው አጭር እስትንፋስ ጋር አንድ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)