am_tn/psa/039/001.md

1.5 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

ኤዶታም

ከዳዊት የሙዚቃ አለቆች ለአንዱ ይህ ተመሳሳይ ስም ነበረው። ይህ ምናልባት እርሱን ያመለክት ይሆናል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚናገረው ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) የመዝሙሩ ስልት የዳዊትን መዝሙር ይመስላል የሚሉት ናቸው።

የምናገረውን አያለሁ

እዚህ ጋ “ማየት” የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን “ልብ ማለት” የሚል ትርጉም አለው። አ.ት፡ “ለምናገራቸው ነገሮች ትኩረት እሰጣለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በምላሴ ኃጢአትን እንዳልሠራ

እዚህ ጋ “ምላስ” የሚያመለክተው የጸሐፊውን ንግግር ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ነገር እንዳልናገር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ልጓም

“መለጎም” ማለት አፍን መዝጋት ነው። ዳዊት እዚህ ጋ የሚናገረው ከክፉ ሰው ጋር ሲሆን እንደማይናገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)