am_tn/psa/038/001.md

1.3 KiB

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚናገረው ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) የመዝሙሩ ስልት የዳዊትን መዝሙር ይመስላል የሚሉት ናቸው።

በቁጣህ አትገስጸኝ … በመዓትህ አትቅጣኝ

በመሠረቱ የእነዚህ ሐረጎች ትርጉም ተመሳሳይ ሲሆን አሳቡ የተደጋገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው። (See: Paral- lelism)

ፍላጻዎችህ ወግተውኛል

በጸሐፊው ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ከባድነት ልክ እግዚአብሔር በጸሐፊው ላይ ቀስት የወረወረበት ያህል ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “ቅጣትህ በቀስት የወጋኸኝ ያህል አሳምሞኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እጅህ ወደ ታች ይጫነኛል

እግዚአብሔር ጸሐፊውን የቀጣበት መንገድ ልክ በእጁ የመታው ያህል ተቆጥሮ ተነግሯል። እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። አ.ት፡ “ኃይልህ መትቶ ይጥለኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)