1.4 KiB
1.4 KiB
የእግዚአብሔር ሕግ በልቡ አለ
እዚህ ጋ “በልቡ ውስጥ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ጥልቅ የሆነውን ውስጣዊ ማንነቱን ነው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በውስጣዊ ማንነቱ ውስጥ ያስቀምጠዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግሮቹም አይንሸራተቱም
እዚህ ጋ እግዚአብሔርን ያለመታዘዝ ከትክከለኛው መንገድ መንሸራተትና መውደቅ እንደሆነ ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንዲሄድበት በሚፈልገው መንገድ በሰላም ይሄዳል” ወይም “እግዚአብሔር እንዲያደርግ የፈለጋቸውን ነገሮች በሰላም ያደርጋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አመጸኛው ሰው … ጻድቁን ሰው … ክፉው ሰው
እነዚህ ተለይተው የታወቁ ሰዎች አይደሉም። በጥቅሉ እንዲህ ዓይነቶቹን ሰዎች የሚያመለክቱ ናቸው። (See: Generic Noun Phrases)
ጻድቁን ሰው ይመለከተዋል
እዚህ ጋ መመልከት ጻድቅ የሆኑትን ሰዎች ለመጉዳት መከታተልን ያመለክታል። አ.ት፡ “ጻድቁን ሰው አድፍጦ ይጠብቀዋል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)