am_tn/psa/037/022.md

3.6 KiB

እነዚያ በእግዚአብሔር የተባረኩ ምድርን ይወርሳሉ፤ በእርሱ የተረገሙት እነዚያ ይቆረጣሉ

ይህ የሁለት ተመሳሳይ አሳቦች ንጽጽር ነው። እነዚያ በእግዚአብሔር የተባረኩት በእግዚአብሔር ከተረገሙት ጋር ተነጻጽረዋል። (See: Parallelism)

እነዚያ በእግዚአብሔር የተባረኩ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነዚያ እግዚአብሔር የሚባርካቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ምድርን ይወርሳሉ

ምድርን መውረስ ርስትን እንደ መቀበል ሆኖ ተነግሯል። ይህንን በመዝሙር 37፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ምድሪቱን እንደ ግል ንብረታቸው አድርገው ይቀበላሉ” ወይም “ምድሪቱ ላይ በሰላም እንዲኖሩ ይፈቀድላቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነዚያ በእርሱ የተረገሙት

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነዚያ እግዚአብሔር የሚረግማቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ይቆረጣሉ

የአመፀኛው መጥፋት ተቆርጦ እንደሚጣል የተክል ቅርንጫፍ ሆኖ ተነግሯል። ይህንን በመዝሙር 37፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሰው አካሄድ የሚጸናው በእግዚአብሔር ነው … በእግዚአብሔር ፊት ይመሰገናል

እነዚህ የአስተሳሰቡን ተገቢነት በሚያሳዩበትና ተደራጊ አንቀጹን በሚያብራሩበት ሁኔታ ሊነገሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት በሚመሰገንበት ሁኔታ ከኖረ እግዚአብሔር አካሄዱን ያጸናለታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የሰው አካሄድ የሚጸናው በእግዚአብሔር ነው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችለው እግዚአብሔር ነው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አንድ ሰው … ሰውየው

ይህ ሰዎችን በአጠቃላይ እንጂ አንድን የተለየን ሰው አያመለክትም። (See: Generic Noun Phrases)

የሰው አካሄድ

አካሄድ የሚወክለው የአንድን ሰው አኗኗር ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው የሚኖርበት አኗኗር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቢደናቀፍም አይወድቅም

እዚህ ጋ “መደናቀፍ” እና “መውደቅ” የሚያመለክቱት ሰውየው በአስቸጋሪ ጊዜ የሚኖረውን ምላሽ ነው። አ.ት፡ “አስቸጋሪ ጊዜዎች ቢገጥሙትም ፈጽሞ አይወድቅም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእጁ ይይዘዋል

እዚህ ጋ “በእጁ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ሲሆን “ይይዘዋል” የሚያመለክተው የሚያደርግለትን ጥበቃ ነው። አ.ት፡ “በኃይሉ ይጠብቀዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)