am_tn/psa/037/016.md

1.2 KiB

ከብዙ ክፉ ሰዎች ሀብት ይልቅ ለጻድቁ ያለው ትንሹ ይሻላል

“ከብዙ ብልጽግና ጋር ክፉ ከመሆን ጻድቅ ሆኖ ድኻ መሆን ይሻላል”

ለጻድቁ ያለው ትንሹ ይሻላል

“ትንሹ” የሚለው ስማዊ ቅጽል የሚያመለክተው ጥቂት ሀብትን ነው። “ጻድቁ” የሚለው ስማዊ ቅጽል የሚያመለክተው ደግሞ ጻድቁን ሰው ነው። አ.ት፡ “ጻድቅ ሰው ያለው ጥቂት ሀብት ይሻላል” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

ብዙ

ይህ የሚያመለክተው የክፉ ሰዎችን ብልጽግና ነው። (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

የክፉ ሰዎች ክንድ ይሰበራል

እዚህ ጋ “ክንድ” የሚወክለው የክፉ ሰዎችን ኃይል ነው። ክንዳቸውን መስበር ሥልጣናቸውን መውሰድን ይወክላል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የክፉ ሰዎችን ብርታት ያስወግዳል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)