am_tn/psa/037/014.md

1.6 KiB

ክፉው

ይህ ክፉዎቹን ሰዎች ያመለክታል። አ.ት፡ “ክፉዎቹ ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

ሰይፋቸውን መዘዋል … ቀስታቸውን ገትረዋል

“ሰይፍ” እና “ቀስት” ሁለቱም ሰዎችን ለማጥቃት ጥቅም ላይ የሚውሉ የጦር መሣሪያዎች ናቸው። “መዘዋል” እና “ገትረዋል” የሚሉት የእርግጠኝነት ቃላት ውጊያውን ለመጀመር ዝግጁ ናቸው ማለት ነው። (See: Synecdoche)

ለመጣል

የእነዚህ ችግረኞች ጥፋት፣ መሬት ላይ ሲጣል ስብርብሩ እንደሚወጣ ሸክላ ማሰሮ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ለማጥፋት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የተጨቆኑና የተቸገሩ

እነዚህ ሁለቱም ቃላት የሚያመለክቱት ራሳቸውን ለመከላከል አቅም የሌላቸውን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “ሊቋቋሟቸው የማይችሏቸው ሰዎች” (See: Doublet)

ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል

ሰይፍ የጦር መሣሪያዎች ምሳሌ ሲሆን “ልብ” የሚወክለው ሕዝቡን ነው። “ልብን መውጋት” በአነጋገር ዘይቤ “መግደል” የሚል ትርጉም አለው። አ.ት፡ “ሰይፋቸው በራሳቸው ላይ ይመለሳል፣ ራሳቸውንም ይገድላሉ” (Synecdoche እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)