am_tn/psa/037/005.md

1.3 KiB

መንገድህን ለእግዚአብሔር ስጥ

እዚህ ጋ “መንገድህን ስጥ” የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን እግዚአብሔር ሕይወትህን እንዲቆጣጠር ጠይቀው ማለት ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አኗኗርህን እንዲመራ ጠይቀው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ስለ አንተ ሆኖ ያደርጋል

ይህ በሕግ ጉዳዮች ሌላውን ሰው መወከል ነው። እዚህ ጋ፣ አንድ ሰው በእግዚአብሔር በሚታመንበት ጊዜ እርሱ ለዚያ ሰው ተከላካይ ይሆናል፣ ፍትሕ እንዲያገኝም ያደርጋል። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እንደ ቀን ብርሃን … ቀትሩም እንደ ቀን

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች የሚሉት ስለ አንድ ነገር ነው። (See: Parallelism)

እንደ ቀን ብርሃን

ይህ “ሁሉም በሚያየው ሁኔታ” ማለት ነው። አ.ት፡ “እንደ ቀን ብርሃን በግልጽ የሚታይ” (See: Simile)

ቀትሩም እንደ ቀን

ይህ “የቀትር ፀሐይ እንደሚታይ” ማለት ነው። አ.ት፡ “በቀን ውስጥ ብርሃኑ ብሩህ ሆኖ እንደሚታይ” (See: Simile)