am_tn/psa/037/001.md

1017 B

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚመለከተው ዳዊትን ነው ወይም 3) መዝሙሩ የዳዊትን መዝሙሮች ዘይቤ የተከተለ ነው የሚሉት ናቸው።

በክፉ አድራጊዎች ምክንያት አትበሳጭ

“አመፀኞች ሰዎች እንዲያናድዱህ አትፍቀድላቸው” ወይም “አመፀኞች ሰዎች በሚያደርጉት ነገር አሳብ አይግባህ”

እንደ ሣር ይደርቃሉ … እንደ አረንጓዴ ተክሎች ይጠወልጋሉ

ክፉ አድራጊዎች በሞቃት የአየር ጠባይ እንደሚደርቅና እንደሚሞት ሣርና ተክል ተደርገው ተነግረዋል። የእነዚህ የሁለቱም ማነጻጸሪያዎች ትርጉም ይሞታሉ የሚል ነው። አ.ት፡ “ይሞታሉ” ወይም “ፍጻሜአቸው ይሆናል” (See: Simile and Parallelism)