am_tn/psa/036/010.md

2.0 KiB

አንተን ለሚያውቁ የኪዳንህን ታማኝነት በሙላት ይድረሳቸው

ያህዌ ዘወትር ለሕዝቡ ታማኝ መሆኑን ወደ እነርሱ እስኪደርስ የሚረዝም ነገር እንደሆነ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የሚለውን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሚያውቁህ በታማኝነት ፍረድላቸው››

ልባቸው ለቀና መከታ ሁንላቸው

‹‹መከታ›› የሚለውን እንደ ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ ካለፈው ሐረግ፣ ‹‹ዘወትር›› የሚለው ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ልባቸው የቀናውን ዘወትር መከታ ሁንላቸው››

ልባቸው የቀና

‹‹ልብ›› ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቅኖች›› ወይም፣ ‹‹በጽድቅ የሚኖሩ ሰዎች››

የእብሪተኛ እግር… የክፉ ሰው እጅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እግር›› እና፣ ‹‹እጅ›› ክፉ ሰዎችን ያመለክታሉ፡፡ እነዚህ ክፉ ሰዎችን በአጠቃላይ እንጂ፣ የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ የሚመለከቱ አይደሊም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እብሪተኛ ሰዎች… ክፉ ሰዎች››

አያሳድደኝ

‹‹አያባርረኝ›› ወይም፣ ‹‹ስፍራዬን እንድተው አያድርገኝ››

ክፉ አድራጊዎች ወድቀዋል፤ ተፈጥፍጠዋል መነሣትም አይችሉም

ሦስቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት የተሸነፉትን ክፉ አድራጊዎች ነው

ተፈጥፍጠዋል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፈጥፍጠሃቸዋል›› ወይም፣ ‹‹አጥፍተሃቸዋል››

መነሣትም አይችሉም

‹‹ከእንግዲህ አይነሡም››