am_tn/psa/036/007.md

1.8 KiB

የኪዳን ታማኘነትህ ምንኛ የከበረ ነው

‹‹የከበረ›› የሚለው ጸሐፊው የያህዌን ኪዳን ታማኝነት ምን ያህል ታላቅ ዋጋ እንደሚሰጠው ያመለክታል›› ‹‹ታማኝነት›› የሚለውን የነገር ስም በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለኪዳንህ ታማኝ መሆንህን ታላቅ ዋጋ እሰጣለሁ››

በቤትህ ሙላት ደስ ይላቸዋል፡፡

ቤት ውስጥ በእንግድነት መመገብ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን ሁሉ መስጠት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ስለምትሰጣቸው ሁሉም አላቸው›› ወይም፣ ‹‹ብዙ የምትሰጠው አለህ፤ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ታዘጋጅላቸዋለህ››

ከደስታህ ወንዝ እንዲጠጡ አደረግህ

እዚህ ላይ ሁለት ምሳሌያዊ ገለጻዎች ቀርበዋል፡፡ የእግዚአብሔር በረከት ሙላት ወንዝ ውስጥ እንደሚፈስስ ውሃ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እነዚህን በረከቶች የሚቀበሉ እንደ ውሃ እየጠጧቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የከበሩ በረከቶችህ እንደሚጠጡት የወንዝ ውሃ ነው››

የሕይወት ምንጭ

‹‹የሕይወት መገኛ››

በብርሃንህ ብርሃን እናያለን

‹‹ብርሃን›› የእውነተኛ ዕውቀት ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ስታበራልን እውነትን እናውቃለን›› ወይም፣ ‹‹ስለ አንተ እውነቱን ማወቅ የሚስችለን የአንተ ብርሃን ነው››