am_tn/psa/036/005.md

1.3 KiB

የኪዳን ታማኝነትህ… ወደ ሰማያት ይደርሳል

የእግዚአብሔር ኪዳን ታማኝነት ወደ ሰማይ የሚደርስ አንዳች ነገር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የሚለውን የነገር ስም በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኪዳን ታማኝነትህ… በጣም ትልቅ ነው›› ወይም፣ ‹‹ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል አንተም… ለኪዳንህ ታማኝ ነህ››

ወደ ደመናት ይደርሳል

የእግዚአብሔር ታማኝነት ትልቅነት በጣም ከፍ ያለ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ደመናት ከፍ ያለ ነው›› ወይም፣ ‹‹እጅግ ታላቅ ነው››

እንደ የእግዚአብሔር ተራሮች… እንደ ታላቁ ጥልቅ

የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍርድ ታላቅነት በጣም ከፍ ያለና የጠለቀ መሆኑን ይህ ሐረግ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ተራሮች ከፍ ያለ… እንደ ባሕር የጠለቀ››

የጠበቅኸው

‹‹የረዳኸው›› ወይም፣ ‹‹ያዳንኸው››