am_tn/psa/036/001.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

‹‹ይህ የመዝሙር መሪው በአምልኮ የሚጠቀምበት ነው››

የያህዌ ባርያ የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት፣ 1) መዝሙሩን የጻፈ ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ክፉ ሰው

ይህ በአጠቃላይ ስለ ክፉ ሰዎች እንጂ፣ ስለ አንድ ሰው የተነገረ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ ሰዎች››

በጥልቅ ልቡ

‹‹ልብ›› የሰውን ጥልቅ ማንነት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከጥልቅ ልቦናው››

በዐይኑ ፊት

‹‹ዐይኑ›› ክፉውን ሰው ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእርሱ ዘንድ››

እንዲህ በማሰብ ራሱን ያጽናናል

‹‹ይህን ማመን ይመርጣል›› ወይም፣ ‹‹እንዲህ ማሰብ ይፈልጋል››

ኀጢአቱ የሚታወቅና የሚጠላ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ኀጢአቱን የሚያውቅና የሚጠላ››