am_tn/psa/035/024.md

2.4 KiB

በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው

‹‹በእኔ መከራ ደስ አይበላቸው››

በልባቸውም አይበሉ

ይህ ለራስ መናገርን የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለራሳቸው አይበሉ››

አሃ

ይህ አንድ ነገር በድንገት ሲደረግ ወይም መግለጽ ሲያቅት የሚባል ቃለ አጋኖ ነው፡፡ ለሚከተለው ነገር አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አዎን››

የፈለግነውን አገኘን

ይህ የሚያመለክተው የጸሐፊው ጠላቶች በደለኛ እንዲባል ፈልገው እንደ ነበር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ፈለግነው በደለኛ ተባለ››

ዋጥነው

የጸሐፊው ጠላቶች የእርሱን ውድቀት እንደ ዱር እንስሳት እርሱን እንደበሉት ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጨርሶ ዋጥነው›› ወይም፣ ‹‹አጠፋነው››

በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፣ ግራም ይጋቡ

‹‹የእኔ መጨነቅ ደስ የሚላቸው ይፈሩ ግራ ይጋቡ››

ይፈሩ

‹‹እፍረት ይከናነቡ››

ግራ ይጋቡ

‹‹የሚያደርጉት ይጥፋቸው›› ወይም፣ ‹‹ይዋረዱ››

ራሳቸውን ከፍ የሚያደርጉብኝ እፍረትና ውርደት ይከናነቡ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ላይ ከፍ ማለት የሚፈለጉትን አንተ እፍረትና ውርደት አከናንባቸው››

እኔ ላይ ከፍ ማለት የሚፈልጉ

‹‹ከእኔ የበለጠ እንደሆኑ የሚቆጥሩ›› ወይም፣ ‹‹እኔ ላይ ክፉ የማድረግ መብት እንዳላቸው የሚያስቡ››

እፍረትና ውርደት ይከናነቡ

እፍረትና ውርደት እንደ ልብስ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ እነዚህን የነገር ስሞች እንደ ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይፈሩ ይዋረዱ››

እፍረት ውርደት

እነዚህ ቃሎች የሚናገሩት ስለ ተመሳሳይ ነገር ቢሆንም፣ ጥቅም ላይ የዋሉት ወርደታቸው የከፋ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡