am_tn/psa/035/009.md

980 B

በማዳኑ

‹‹ማዳን›› የሚለውን የነገር ስም እንደ ግሥ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ስላዳንኸኝ››

ዐጥንቶቼ ሁሉ

‹‹ዐጥንት›› የሰውየውን ጥልቅ ውስጣዊ ማንነት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠቅላላ ውስጣዊ ማንነቴ››

ያህዌ እንደ አንተ ማን አለ… ሊቀሟቸው ከሚሞክሩ?

የዚህ ጥያቄ መልስ እንደ ያህዌ ማንም የለም የሚል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ እንደ አንተ ማንም የለም ሊቀሟቸው ከሚሞክሩ››

ድኾችና ችግረኞች

‹‹ድኾች›› እና፣ ‹‹ችግረኞች›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ አጽንዖት የተሰጠው ርዳታውን የሚፈልጉትን ብዙዎች ያህዌ እንደሚያድናቸው ነው፡፡