am_tn/psa/034/018.md

1.2 KiB

ያህዌ ቅርብ ነው

‹‹ቅርብ›› ማለት ‹‹ለመርዳት ዝግጁ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ዘወትር ለመርዳት ዝግጁ ነው››

ልባቸው የተሰበረ

ይህ ልባቸው የተሰበረ ሰዎችን የማያመለክት አነጋገር ነው፡፡ ጥልቅ ሐዘን የሰውን ልብ መሰበር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ያዘኑ ሰዎች››

መንፈሳቸው የደቀቀ

በጣም ተስፋ የቆረጡ ሰዎች መንፈሳቸው የደቀቀ ሰዎች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ተስፋ የቆረጡ ሰዎች››

ጻድቃን

ይህ የሚያመለክተው ጻድቅ ሰዎችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጻድቅ ሰዎች››

ዐጥንቱን ሁሉ ይጠብቃል፤ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም

‹‹ዐጥንቱ ሁሉ›› ቃል በቃል ቢሆንም፣ ያህዌ መላውን ሰው እንደሚጠብቅም ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ፈጽሞ ይጠብቀዋል፤ በምንም መንገድ ጉዳት አያገኘውም››