am_tn/psa/034/015.md

1.2 KiB

የያህዌ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው

‹‹የያህዌ ዐይኖች›› በጥንቃቄ መጠበቁን ያመለክታል፡፡ ‹‹ጻድቃን›› ጻድቅ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ጻድቅ ሰዎችን በጥንቃቄ ይጠብቃል››

ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው

ያህዌ፣ ‹‹በጆሮዎቹ›› ተወክሏል፡፡ ለአንድ ነገር ክፍት መሆን ለዚያ ነገር ትኩረት መስጠትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለጩኸታቸው ትኩረት ይሰጣል›› ወይም፣ ‹‹ለጩኸታቸው መልስ ይሰጣል››

መታሰቢያቸውን ከምድር ይቆርጣል

ልክ በቢላ ተቆርጦ የተጣለ ይመስል እነርሱ ሲሞቱ ያህዌ መታሰቢያቸውን ጨርሶ ያጠፋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሲሞቱ ሰዎች ጨርሶ ይረሷቸዋል››

ያህዌ ይሰማል

‹‹ይሰማል›› ማለት ምላሽ ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ትኩረት ይሰጣቸዋል››