am_tn/psa/034/012.md

1.5 KiB

መልካምን እንዲያይ ሕይወትን የሚፈልግና ረጅም ዘመን መኖር የሚፈልግ ማን ነው?

ለዚህ ጥያቄ መልሱ፣ ‹‹ሰው ሁሉ›› የሚል ነው፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰው ሁሉ ሕይወትንና ረጅም ዕድሜ መኖርን እንዲሁም መልካምን ነገር ማየትን ይፈልጋል››

አንደበትህን ከክፉ ጠብቅ… ከንፈሮችህን ሐሰት ከመናገር ከልክል

እነዚህ ሁለት ሐረጐች ተመሳሳይ ነገር ማለት ቢሆኑም ለአስፈላጊነቱ አጽንዖት ለመስጠት በሁለት የተለያዩ መንገዶች ቀርቧል፡፡

አንደበትህን ከክፉ ጠብቅ

‹‹አንደበት›› መላውን ሰው ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ አትናገር››

ከንፈሮችህን ሐሰት ከመናገር ከልክል

‹‹ከንፈር›› የሚናገረውን ሰው ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሐሰት አትናገር››

ከክፉ ሽሽ

‹‹ሽሽ›› ከክፉ ራቅ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ አታድርግ››

ሰላምን እሻ

‹‹እሻ›› ስለ ሰላም አስብ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሰዎች ጋር በሰላም ለመኖር አጥብቀህ ፈልግ››