am_tn/psa/033/020.md

954 B

ያህዌን እንጠባበቃለን

‹‹መጠባበቅ›› መተማመን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ እንታመናለን›› ወይም፣ ‹‹ያህዌን ተስፋ እናደርጋለን››

እርሱ ረዳታችን፣ ጋሻችንም ነው

እዚህ ላይ ያህዌ ሰራዊትን ከጥቃት የሚከልል ጋሻ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ረዳታችንና እንደ ጋሻ የሚከልለን ነው››

ልባችን ደስ ይለዋል

‹‹ልብ›› የሚያመለክተው ሕዝቡን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ደስ ይለናል››

በቅዱስ ስሙ

‹‹ቅዱስ ስሙ›› የያህዌን ቅዱስ ባሕርይ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቅዱስ ባሕርዩ›› ወይም፣ ‹‹እርሱ ቅዱስ ስለሆነ በእርሱ››