am_tn/psa/033/010.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እያንዳንዱ ቁጥር በጣም የሚመሳሰሉ ትርጒሞች ያሏቸው ሁለት መስመሮች ይዞአል፡፡

ያህዌ ያጨናግፋል

‹‹ያህዌ ያጠፋል›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይሰብራል››

የሕዝቦች ወገን

‹‹ሕዝቦች›› የእነዚህ አገሮችን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የተለያዩ ሕዝቦች ወገን››

ኅብረት

ኅብረት በጦርነት ጊዜ አብረው የጋራ ጠላት እንዲወጉ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ወገኖች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡

የሕዝቦች ምክክር

‹‹የሰዎች ፍላጐት›› አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰዎች ክፉ ምክክር››

ለዘላለም ይጸናል

‹‹ይጸናል›› ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን፣ ‹‹ይኖራል›› ማለት ነው፡፡

ለትውልዶች ሁሉ የልቡ ሐሳብ

‹‹ይጸናል›› የሚለው ቃል ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የልቡም ሐሳብ ለትውልዶች ሁሉ ይጸናል››

የልቡም ሐሳብ

‹‹ልብ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእርሱ ሐሳብ››

ለትውልዶች ሁሉ

‹‹ወደ ፊት ለሚኖሩ ትውልዶች ሁሉ›› ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን፣ ‹‹ለዘላለም›› ማለት ነው፡፡

ሕዝብ የተባረከ ነው

‹‹ሕዝብ›› ሲል ሰዎችን ሁሉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች የተባረኩ ናቸው››

ያህዌ አምላኩ የሆነ

‹‹ያህዌን የሚያመልክ››

እንደ ራሱ ርስት

እዚህ በተገለጸው መሠረት የእርሱ ርስት የሆኑ ይመስል ሕዝቡ ያህዌን እንዲያመልኩ ተመርጠዋል፡፡