am_tn/psa/033/004.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እያንዳንዱ ቁጥር በጣም ተመሳሳይ ትርጒም ያላቸው ሁለት መስመሮች አሉት፡፡

የያህዌ ቃል የቀና ነው

‹‹የቀና›› የሚለው እውነተኛ የሆነ ነገርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ሁሌም አደርጋለሁ ያለውን ያደርጋል››

ጽድቅንና ፍትሕን ይወድዳል

እነዚህን የነገር ስሞች በተግባር መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጽድቅና እውነት የሆነውን ነገር ማድረግ ይወድዳል›› ወይም፣ ‹‹ጽድቅና እውነት የሆነውን ነገር የሚያደርጉትን ይወድዳል››

ምድር በያህዌ ኪዳናዊ ታማኝነት ተሞልታለች

በዓለም ማንኛውም ቦታ ያሉ ሰዎች የያህዌን ኪዳናዊ ታማኝነት ማስረጃ ማየት መቻላቸው ኪዳናዊ ታማኝነቱ ምድርን እንደ ሞላ ተነግሯል፡፡ ‹‹ኪዳናዊ ታማኝነት›› የሚለውን የነገር ስም እንደ ቅጽል መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር የትኛውም ቦታ ያሉ ሰዎች ያህዌ ለኪዳኑ ታማኝ መሆኑን ማየት ይችላሉ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ለኪዳኑ ታማኝ ስለ መሆኑ በምድር ሁሉ ማስረጃ አለ››

በያህዌ ቃል ሰማያት ተሠሩ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቃሉ አማካይነት ያህዌ ሰማያትን ሠራ››

በአፉ እስትንፋስ

ይህ የሚያመለክተው የያህዌን ቃል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቃሉ››