am_tn/psa/032/009.md

1.5 KiB

ማስተዋል እንደሌላቸው… እንደ ፈረስ አትሁኑ

ጸሐፊው ማስተዋል የሌላቸውን ሰዎች ከፈረስና ከበቅሎ ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ ይህም ማለት፣ 1) ጸሐፊው ለአንባቢዎቹ የያህዌን ቃል እየተናገረ ነው፤ ‹‹ሁላችሁም ማስተዋል እንደሌላቸው… እንደ ፈረስ አትሁኑ›› ወይም 2) ለብዙዎች እንደሚናገር ያህዌ ለጸሐፊው እየተናገረ ነው፡፡

በልባብና በልጓም

ሁለቱም ነገሮች ፈረሶችና በቅሎዎች እንዲሄዱ ወደሚፈልጉት ቦታ ለመምራት የሚጠቀሙባቸው ናቸው፡፡

እንዲሄዱ የምትፈልገው

‹‹ሰው ሁሉ እንዲሄዱ የሚፈልገው›› እዚህ ላይ፣ ‹‹አንተ›› ነጠላ ቁጥር ቢሆንም፣ አንድን ሰው ነጥሎ እየተናገረ አይደለም፡፡

የያህዌ ኪዳናዊ ታማኝነት የሚታመንበትን ይከብበዋል

ያህዌ ለሰው ታማኝ መሆኑና እርሱንም መጠበቁ የያህዌ ኪዳናዊ ታማኝነት ያንን ሰው እየከበበው እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የሚለው የነገር ስም እንደ ቅጽል ሊተረጐም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ለኪዳኑ ታማኝ በመሆኑ፣ በእርሱ የታመነውን ይጠብቀዋል››