am_tn/psa/032/001.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት 1) መዝሙሩን የጻፈ ዳዊት ነው፡፡ ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ማስቺል

ይህ የአዘማመርን ስልት የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡

መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ ኀጢአቱም የተሸፈነለት

እነዚህ ሐረጐች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፡፡ በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር መተላለፉን ይቅር ያለው፣ ኀጢአቱንም የሸፈነለት››

ኀጢአቱ የተሸፈነለት

ይቅር የተባለ ኀጢአት ከእንግዲህ ማንም እንዳያየው የተሸፈነ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአቱ የታለፈለት›› ወይም፣ ‹‹ሆን ተብሎ ኀጢአቱ የተረሳለት››

ያህዌ በደሉን የማይቆጥርበት

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ እንደ ንጹሕ የሚያየው›› ወይም፣ ‹‹በያህዌ ፊት በደለኛ ያልሆነ››

በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት

‹‹መንፈስ›› የሚያመለክተው ሰውየውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሽንገላ የሌለበት›› ወይም፣ ‹‹ፍጹም ቅን የሆነ››