am_tn/psa/031/019.md

1.7 KiB

በጐነትህ

ይህን ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ የምታደርገው መልካም ነው››

ያስቀመጥሃት

የያህዌ በጐነት እንደ አንዳች ነገር የሚቀመጥ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ለሚያስፈልግ ጊዜ ያስቀመጥኸው››

ለሚፈሩህ

‹‹አንተን በጣም ለሚያከብሩ››

ወደ አንተ ለሚጠጉ

ጥበቃ ለማግኘት ወደ ያህዌ መሄድ ወደ እርሱ መጠጋት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ መዝሙር 31፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥበቃ እንድታደርግላቸው ወደ አንተ ለሚመጡ››

በማደሪያህ ውስጥ ትሸሽጋቸዋለህ… በመጠለያህ ውስጥ ትደብቃቸዋለህ

ሁለቱም ሐረጐች እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል ማለት ናቸው፡፡

በመጠለያህ

የያህዌ ማደሪያ ጸሐፊው ደህንነት የሚያገኝበት ትልቅ ግንብ እንደሆነ ተነግሯል

በመጠለያህ ትደብቃቸዋለህ

እዚህ ላይ፣ ‹‹መጠለያ›› አደጋ የሌለበት ቦታ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አደጋ የሌለበት ቦታ ታዘጋጅላቸዋለህ››

ከአንደበት ጭቅጭቅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አንደበት›› ጸሐፊው ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቻቸው ክፉ መናገር የማይችሉበት››