am_tn/psa/031/014.md

843 B

ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው

‹‹በእጅህ›› የያህዌን ኀይል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የወደ ፊት ሕይወቴን ለመወሰን ኀይል አለህ››

ለሚያሳድዱኝ

‹‹ሊይዙኝ ለሚሞክሩ››

ባርያህ ላይ ፊትህን አብራ

ያህዌ ለእርሱ መልካም ነገር ማድረጉ እርሱ ላይ ፊቱን ማብራት እንደሆነ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለባርያህ መልካም አድርግ››

በኪዳናዊ ታማኝነትህ አድነኝ

‹‹ታማኝነት›› የሚለውን የነገር ስም እንደ ቅጽል መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለኪዳንህ ታማኝ በመሆንህ አድነኝ››