am_tn/psa/031/005.md

1.8 KiB

በእጆችህ

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ እዚህ ላይ ግን እጅ እንዳሉት ተነግሯል፡፡ ‹‹እጆችህ›› የሚለው የያህዌን ጥበቃ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹ለጥበቃህ››

መንፈሴን እሰጣለሁ

‹‹መንፈሴ›› የሚለው የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሴን አኖራለሁ››

የሚታመን አምላክ

‹‹አንተ የምታመንብህ አምላክ ነህ››

ከንቱ ጣዖቶች የሚያገለግሉትን ጠላሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ከንቱ›› የሚለው ጣዖቶችን ሁሉ ይመለከታል፡፡ ይህን በትርጒም ማብራራት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጣዖቶች ከንቱ ናቸው፤ እነርሱን የሚያገለግሉትን ጠላሁ››

በኪዳናዊ ታማኝነትህ ደስ ይለኛል፤ ሐሤት አደርጋለሁ

‹‹ደስታ›› እና፣ ‹‹ሐሤት›› የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ ትርጒም ቢኖራቸውም፣ የደስታውን ታላቅነት አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የሚለውን የነገር ስም እንደ ቅጽል መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ለኪዳንህ ታማኝ ስለሆንህ በጣም ደስ ይለኛል››

መከራዬን አይተሃል… የነፍሴንም ጭንቀት አውቀሃል

ሁለቱም ሐረጐች እግዚአብሔር የጸሐፊውን መከራ እንደሚያውቅ ያመለክታሉ፡፡

የነፍሴን ጭንቀት

‹‹ነፍሴ›› ጸሐፊውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹‹‹ጭንቀቴን››