am_tn/psa/031/003.md

1.4 KiB

ዐለቴ

ያህዌ ጸሐፊውን ከጥቃት የሚያድን ግዙፍ ዐለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምድንበት ግዙፍ ዐለት››

ምሽጌ

ያህዌ ጸሐፊው ከጠላቶቹ የሚድንበት ጠንካራ ምሽግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ስለ ስምህ ስትል

‹‹ስም›› የሚወክለው ያህዌን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስምህ እንዲከበር›› ወይም፣ ‹‹እኔ እንዳመልክህ››

ምራኝ መንገዱን አመልክተኝ

‹‹ምራኝ›› እና፣ ‹‹አመልክተኝ›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ ያህዌ እንዲረዳው ያቀረበውን ልመና ያጠነክራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድሄድ ወደምትፈልገው ምራኝ››

ከሰወሩብኝ መረብ አወጣኝ

ጸሐፊው በተሰወረ መረብ እንደ ተያዘ ወፍ እንደሆነና ያህዌ ከወጥመዱ ነጻ እንዲያደርገው እንደሚጠብቅ ይናገራል፡፡

አንተ መጠጊያዬ ነህ

ያህዌ ሰዎች ጸሐፊውን እንዳያጠቁ የሚደበቅበት ቦታ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ሁሌም ትጠብቀኛለህ›› ወይም፣ ‹‹ዘወትር ጥበቃ ታደርግልኛለህ››