am_tn/psa/031/001.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

‹‹ይህ በአምልኮ ጊዜ ለመዘምራን መሪ ነው››

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት፣ 1) መዝሙሩን የጻፈ ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው፡፡

ያህዌ ሆይ፣ በአንተ እሸሸጋለሁ

ጥበቃ እንዲደረግለት ወደ ያህዌ መሄድ እርሱ ውስጥ መሸሸግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድትጠብቀኝ ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እሄዳለሁ››

አታሳፍረኝ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌሎች እንዲያሳፍሩኝ አታድርግ››

መጠጊያ ዐለቴና የምታድነኝ ምሽግ ሁነኝ

‹‹መጠጊያ ዐለቴ›› ማለት ጥበቃ እንዲያገኝ መለመን ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ሐረግ የመጀመሪያውን ሐረግ ያጠናክራል፡፡

መጠጊያ ዐለቴ

የሚያድን ታላቅ ዐለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔን እንደሚያድን ግዙፍ ዐለት››

የምታድነኝ ምሽግ

ያህዌ ጸሐፊው ከጠላቶቹ የሚድንበት ጠንካራ ምሽግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡