am_tn/psa/030/011.md

1.2 KiB

ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ

በጣም ደስ ሲላቸው ማሸብሸብ በአይሁድ ባሕል የተለመደ ነበር፡፡ ‹‹ዋይታ›› እና ‹‹ማሸብሸብ›› እንደ ግሥ ማቅረብ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዋይታዬን ትቼ ደስ ብሎኝ እንዳሸበሽብ አደረግህ››

ማቄን አስወገድህ

ማቅ ከዋይታና ከሐዘን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ እንዳላዝን አደረግህ››

ደስታን አለበስኸኝ

ደስታ እንደ ልብስ የሚለበስ ነገር እንደሆነ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ደስ አሰኘኸኝ››

ክብሬ ምስጋናህን ይዘምራል

‹‹ክብሬ›› የሚለው የጸሐፊውን ነፍስ፣ ልብ ወይም ውስጣዊ ሰውነት ያመለክታል፡፡ ይህ ደስ ስላሰኘው እግዚአብሔርን እያመለከ ያለውን የጸሐፊውን ሙሉ ሰውነት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምስጋና እዘምርልሃለሁ››