am_tn/psa/030/009.md

1001 B

በመሞቴና ወደ መቃብር በመውረዴ ምን ጥቅም ይገኛል?

ጸሐፊ ይህን ጥያቄ ያቀረበው የእርሱ መሞት ለእግዚአብሔር ጥቅም እንደሌለው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብሞትና ወደ መቃብር ብወርድ ምንም ጥቅም የለም››

ዐፈር ያመሰግንሃልን? ታማኝነትህንስ ይናገራልን?

ጸሐፊው ይህን ጥያቄ ያቀረበው የእርሱ መሞትና መበስበስ እግዚአብሔርን እንደማያመሰግን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐፈር በእርግጥ አያመሰግንህም፤ ታማኝ መሆንህንም ለሌሎች አይናገርም››

ዐፈር

ይህ የሚያመለክተው ሲሞት ዐፈር የሚሆነውን የጸሐፊውን ሰውነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚበሰብስ አካሌ››