am_tn/psa/030/004.md

1.6 KiB

ቅድስናውን ስታስታውሱ አመስግኑ

‹‹ቅድስና›› እና፣ ‹‹ማመስገን›› የተሰኙትን የነገር ስሞች፣ ‹‹ምስጋና›› እና፣ ‹‹ቅዱስ›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን አስታውሱ ስለዚህ አመስግኑ›› ወይም፣ ‹‹ቅዱስ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር ያደረገውን አስታውሱ፤ ስለዚህ አመስግኑት››

ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው

‹‹ቁጣው የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ነው›› ‹‹ቁጣ›› የሚለውን የነገር ስም፣ ‹‹መቆጣት›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚቆጣው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው››

ለአጭር ጊዜ

‹‹ለአጭር ጊዜ›› ለጊዜው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለጊዜው››

ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው

‹‹ሞገስ›› የሚለውን የነገር ስም፣ ‹‹ቸርነት›› በሚል ቅጽል መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እርሱ ቸር ነው››

ለቅሶ ማታ ይመጣል፤ ደስታ ግን ጠዋት ይመጣል

ይህ፣ ‹‹ለቅሶ›› እና ‹‹ደስታ›› በተወሰነ ጊዜ የሚመጡ ነገሮች እንደሆነ ተነግሯል›› አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማታ እናለቅስ ይሆናል ጠዋት ግን ደስ ይለናል››